ኢትዮጵያ የኒውክሌር ቴክኖሎጂን የዜጎችን ደህንነት በጠበቀ መልኩ እየተጠቀመችበት መሆኑ ተገለፀ

OBN ሐምሌ 26 2011 ኢትዮጵያ የኒውክሌር ቴክኖሎጂን የዜጎችን ደህንነት በጠበቀ መልኩ እየተጠቀመችበት መሆኑ ተገለፀ

ቴክኖሎጂውን ጥቅም ላይ ከማዋል ጎን ለጎን የህብረተሰብ ደህንነትን መጠበቅ ላይ ቅድሚያ ሰጥታ እየሰራች መሆኑ ተነግሯል፡፡

ሀገራት የኒውክሌር ቴክኖሎጂን ለሰላማዊ ጥቅም ለማዋል የገቡትን ቃል እንዴት እያከበሩ ነው በሚለው ላይ ትኩረቱን ያደረገው መድረክ በፊንፊኔ ሲካሄድ ቆይቶ ተጠናቋል፡፡

ቴክኖሎጂው ጥቅም ላይ ሲውል ቁጥጥር ለማድረግ የሚያስችል የፖሊሲ ማሻሻያና ለሰላማዊ ጥቅም ሲውልም የዜጎችን ደህንነት የመጠበቂያ ስልት ውይይቱ አካል ነበሩ፡፡

ሀገራት የኒውክሌር ቴክኖሎጂን ለሰላማዊ ጥቅም ብቻ እያዋሉት ስለመሆኑ ቅኝት የሚያደርግ ቡድን ሲመጣ እንዴት መረጃ መስጠት እንደሚቻልም ተዳሷል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ዴኤታ ጀማል በከር ኢትዮጵያ በፈረመችው ውል መሰረት የኒውክሌር ቴክሎጂን የዜጎችን ደህንነት በጠበቀ መልኩ ለሰላማዊ ጥቅም ብቻ እያዋላችው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ጨረራ መከላከል ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሰለሞን ጌታቸው ቴክኖሎጂውን ለካንስር ህክምና፤ ለቆላ ዝንብ ማምከኛ እና ለመንገድ ስራ በአግባቡ እየተጠቀመችበት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ቴክሎጂው ለማዕድን ፍለጋና ለሃይል ምንጭነትም ጥቅም ላይ ይውላል ተብሏል፡፡
በመደርኩ ከተለያዩ ሀገራት የመጡ ባለሙዎች ተሳትፈውበታል፡፡

 

Facebook Comments