ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ከአክሱም ከተማ ነዋሪዎች ጋር ተወያይተዋል

የአክሱም ሐውልት የኢትዮጵያ ቀደምት ሥልጣኔ ምስክር ነው።

ኦቢኤን ሰኔ 03 2011 – ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ከአክሱም ከተማ ነዋሪዎች ጋር ተወያይተዋል:: ነዋሪዎቹ ጠ/ሚሩ ጥያቄያቸውን ተቀብለው ሐውልቱን በማደስ ዙሪያ ለመነጋገር መምጣታቸውን አድንቀዋል:: ከዚህም በተጨማሪ ጠ/ሚሩ በበጀት ምደባ፣ በውኃ እጥረት፣ በመሠረተ ልማት ጥያቄዎችና በሰላምና ጸጥታ ዙሪያ ከነዋሪዎቹ ጋር ተወያይተዋል::

የአክሱም ሐውልት የኢትዮጵያ ቀደምት ሥልጣኔ ምስክር ነው።

ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድና የልዑካን ቡድናቸው በአሁኑ ወቅት በአክሱም ከተማ በመገኘት ሐውልቱ የሚገኝበትን ሁኔታ ተመልክተዋል።

ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ በሥፍራው ሲደርሱ የትግራይ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ደብረ ጽዮን ገ/ሚካኤል አቀባበል አድርገውላቸዋል።@#PMOffice

Facebook Comments