በኤርፖርት ጉምሩክ ህገወጥ የስናይፐር የጦር መሳሪያ አክሰሰሪዎች ተያዙ

ኦቢኤን ጥቅምት 26፣ 2012- ኤርፖርት ጉምሩክ የግል መገልገያ እቃዎችን ሽፋን በማድረግ በአረቢያን መጅሊስ ውስጥ ተደብቆ የመጡ የስናይፐር የጦር መሣሪያ መለዋወጫ በፍተሻ መያዙ ተነገረ፡፡

በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ የግል መገልገያ እቃዎችን ሽፋን በማድረግ በአረቢያን መጅሊስ ውስጥ በህገወጥ መንገድ ተደብቆ በግለሰብ ስም የመጡ የተለያዩ የስናይፐር የጦር መሣሪያ አክሰሰሪዎች በኤክስሬይ እና በእቃ ፍተሻ ኦፊሰሮች ሊያዝ የቻለ ሲሆን ተጠርጣሪው ግለሰብም በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

ሠላምን ሊያደፈርሱ የሚሠሩ ህገ-ወጥ ተግባራትን ለመከላከል ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የበኩሉን መወጣት አለበት።
@የገቢዎች ሚኒስቴር

Facebook Comments