ቀነኒሳ በቀለ በለንደን ማራቶን ከኪፕቾጌ ጋር ይፎካከራል

ቀነኒሳ በቀለ በለንደን ማራቶን ከኪፕቾጌ ጋር ይፎካከራል

 

 

 

 

ኦብኤን ጥር 8,2012-ኢትዮጵያዊው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ እና ኬንያዊው ኤልዩድ ኪፕቾጌ በዘንድሮው የለንድን ማራቶን ከፍተኛ ፉክክር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል ሲል ቢቢሲ አስነብቧል።

ቀነኒሳ የምንግዜም የዓለም ማራቶን ሁለተኛውን ፈጣን ሰዓት ያስመዘገበ ሲሆን፣ ኪፕቾጌ ደግሞ የዓለም ማራቶን ክብረወሰን ባለቤት ነው።

የ37 ዓመቱ ቀነኒሳ ባሳለፍነው መስከረም በርሊን ላይ ባሸነፈበት ወቅት የኪፕቾጌን የዓለም ማራቶን ክብረወሰን ለመስበር 2 ሰከንዶች ብቻ ነበር የቀሩት።

“ከዚህ ቀደም ከኤልዩድ ኪፕቾጌ ጋር ብዙ ውድድሮችን አድርገናል፤ በቀጣይም እንደምንወዳደር አስባለሁ” ሲል ቀነኒሳ ተናግሯል።

በውድድሩ ኢትዮጵያውያኑ ሞስነት ገረመው እና ሙሌ ዋሲሁን እንደሚሳተፉ ይጠበቃል።

ቀነኒሳ በቀለ እና ኤልዩድ ኪፕቾጌ ከዚህ ቀደም በተገናኙባቸው ሁሉም አይነት 20 ውድድሮች 13ቱን ቀነኒሳ አሸንፏል።

ሁለቱ በተገናኙበት 14 የትራክ ውድድሮች 11ዱን ቀነኒሳ አሸንፏል፡፡

በጎዳና ላይ ሩጫዎች በተገናኙባቸው አራት የማራቶን ውድድሮች ሁሉንም ያሸነፈው ኪፕቾጌ መሆኑን ዘገባው ያስረዳል።

Facebook Comments